የኢትዮጵያ ቱሪዝም ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት 4ኛውን መደበኛ ጉባኤ አካሄደ፣

Newsየአገሪቱን የቱሪዝም ዘርፍ ከነበረበት አዝጋሚ የለውጥ እንቅስቃሴ ወደ እመርታዊ ለውጥ እንዲሸጋገር ከፍተኛ ኃላፊነት ተስጥቶት በሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 294/205 መሠረት የተቋቋመው የኢትዮጵያ ቱሪዝም ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት 4ኛውን መደበኛ ጉባኤ መጋቢት 13 ቀን 2009 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ ሆቴል አካሄደ፡፡

በጉባኤው ለክቡራን እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን በመግለጽ፤ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ክብርት ዶ/ር ሂሩት ወ/ማርያም የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ሲሆኑ፣ ባስተላለፉት መልዕክት የመወያያውን የመነሻ ሀሳብምክር ቤቱ ከተቋቋመበት ዓላማ አንፃር እና ከዚህ ቀደም ባካሄዳቸው ጉባኤያት ያስቀመጣቸው መሰረታዊ አቅጣጫዎች መሠረት ላለፉት ስድስት ወራት  የተከናወኑ ተግባራት ዝርዝር ሪፖርት ለውይይት አቅርበዋል፡፡
 
NEWSበተለይ የቱሪዝም ዘርፉ ከነበረበት አዝጋሚ የለውጥ እንቅስቃሴ ወደ እመርታዊ ለውጥ እንዲሸጋገር ከተቀመጡት ሶስት ፒላሮች በዘርፉ የሰው ኃይል አቅም ግንባታ ረገድ በሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሠልጠኛ ኢንስቲትዩት የ10 ዓመት ፍኖተ ካርታ እንዲኖረው መደረጉንና በመስተንግዶ ተቋማት ውስጥ የሰለጠነ የሰው ኃይል ፍላጎት በሀገር አቀፍ ደረጃ 23 ከመቶ ማሟላት መቻሉን፣ 168 ሆቴሎች ከ1-5 ኮከብ ደረጃ ማግኘት መቻላቸውን፣ የቱሪዝም አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን የውስጥ አቅም ከመደገፍ አኳያ የቀረጥ ነፃ ፈቃድ እየተሰጣቸው ያለ ቢሆንም የተሰጣቸውን ዕድል ያለአግባብ የመጠቀም ሁኔታ የሚታይባቸውን ለይቶ እርምጃ የመውሰድ እንቅስቃሴ መጀመሩን እንዲሁም በቱሪዝም ግብይት፣ በቱሪዝም መዳረሻ ልማት ሥራዎች የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት እና የአክሱም መካነቅርስ ቦታዎች ላይ ውጤታማ የሆኑ ልዩ ልዩ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች እና መጠነኛ ጥገናዎች መካሄዳቸውን፣ በብሔራዊ ፓርኮች የተደቀኑ ችግሮችን ለመቅረፍ በማጎ፣ ማዜ፣ ጊቤ ሸለቆና ሎካ ብሔራዊ ፓርኮች ከማህበረሰቡና ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቶች መካሄዳቸውን ሌሎች ለዘርፉ ልማት ማነቆ የሆኑ አሠራሮችን ለመቅረፍና በእሴት ሰንሰለት ውስጥ እሴት የሚጨምሩ የሕግ ማዕቀፎች ተዘጋጅተው ለሚያፀድቀው አካል ተልከው በውሳኔ ሂደት ላይ መሆኑን በሪፖርታቸው ገልጸዋል፡፡

አክለውም በሀገር አቀፍ ደረጃ በአግባቡ ያልተጠኑ እና ያልለሙ የቱሪዝም መስህቦችን የመለየትና የልማት አማራጮችን ለማስፋት ከምሁራንና ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመመካከር አዳዲስ ፈርጆችን ተግባራዊ ለማድረግ በእስልምና ታሪክ ትልቅ ሥፍራ የሚሰጠውን አልነጃሺ መስጂድን ለሃማኖታዊ ቱሪዝም መዳረሻ እንዲሆን፣ ለመላው አፍሪካውያን አንፀባራቂ የጋራ ታሪካችን በሆነው የአድዋ ተራሮች ታሪካዊ ሙዚየም እንደሚገነባ፣ በኢኮቱሪዝም ዘርፍ በጣና አካባቢና በአባይ ወንዝ መነሻዎች የልማት ስራ፣ በኤርታአሌ እሳተገሞራ ስፍራንና መሰል የጂኦሎጂካል የቱሪዝም መዳረሻዎች የሚለሙበትና ለጎበኚዎች ተደራሽ የሚሆኑበት ሁኔታ እንደሚመቻች አስገንዝበዋል፡፡
   
እንዲሁም ኢትዮጵያን በዓለም ቱሪዝም ገበያ እያስተዋወቀ ያለው አዲሱን መለያ “Ethiopia LAND OF ORIGINS" አቻ የአማርኛ ትርጉም በመውጣቱ በጉባኤው ይፋ ተደርጓል፡፡

News

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ በመለያው አቻ አማርኛ ትርጉሙ ላይ የክብር ፊርማቸውን አኑረዋል፡ በመቀጠል ቀደም ሲል ምክር ቤቱ ባስቀመጣቸው አቅጣጫዎች የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት በአቶ ሰለሞን ታደሰ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ የቀረበ ሲሆን፣ በሪፖርቱ ላይ ውይይት ከመደረጉ በፊት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ በጉባኤው የተገኙትን የክልል መንግስታት ርዕሰ መስተዳድራትን፣ የተለያዩ ተቋማት ሚኒስትሮችን፣ ኮሚሽነሮችንና የሃይማኖት መሪዎችን በማመስገን ላልተገኙትም መልዕክቱ እንዲደርሳቸው በማሳሰብ አጠቃላይ የመወያያ አቅጣጫዎች የመንደሪያ ሀሳቦችን አመላክተው መድረኩን ክፍት አድርገዋል፡

NEWSየምክር ቤቱ አባላትም አዳዲስ ሀሳቦችን፣ ጥያቄዎችንና፣ አስተያየቶችን በማንሳት ጥልቅ ውይይቶች ተካሂደው ቀጣይ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል፡፡

በተለይ ከተቀመጡት አቅጣጫዎች መካከል በቱሪዝም ዘርፉ የሚፈለገው ትራስፎርሜሽን እንዲመጣ የመዳረሻ ልማት ሥራዎች በግል ባለሀብቶች ተሳትፎ መጠናከር ያለበት በመሆኑ እየተሰጡ ያሉ የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ስርዓቶች በተጨማሪ በቦታ ርቀት ምክንያት የግል ባለሀብቱ በማይደርስባቸው የመዳረሻዎች ልማቶች ለኢንቨስትመንት አማራጮች የግል ባለሀብቱን ከፍተኛ ሚና ለማሳደግ የሚያስችሉና ለፖሊሲ አቅጣጫ ግብዓት የሚረዳ የማበረታቻ ሥርዓት በኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት ተጠንቶ እንዲቀርብ፣ ለፖሊሲ አቅጣጫ የሚረዱ አዳዲስ ሀሳቦችን የሚያመጡ የቲንክታንክ ቡድኖችን ከቦርዱ አባላት የማቋቋምና የመደገፍ ሥራ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንዲጠናከር፣ የተቋም አቅም ግንባታ ላይ የተሻሉ ተቋማዊ አደረጃጀቶችን ፈጥረን ከፌዴራል እስከታችኛው እርከን ድረስ በቁልፍ ጉዳይ ተይዞ የማሳካት ሥራ እንዲከናወን፣ ሁሉንም ነገር በተቋም አቅም ይሠራል ማለት ስለማይቻል፣ በተቋማት የሚታዩ የአቅም ክፍተቶችን ለመሙላት እንዲቻል ፕሮፌሽናል ባለሙያ ለማግኘት የሌሎች ተቋማት ምሁራንን እንድንጠቀምበት የተቀመጠውን የጥምረት ቅጥር /Joint Employment system/ ሥርዓት መጠቀም እንደሚቻል፣ በምናካሂዳቸው የመዳረሻ ልማት ሥራዎች፣ የእንክብካቤና ጥገና ሥራዎች ምክንያት የአካባቢውን ስነሕይወታዊ ምህዳር የማያዛባና የማይጎዳ፣ የታሪካዊ ቅርሶች ጥንታዊ  ቅርስነታቸውን መልክና ይዘት የሚቀይርና የሚጎዳ እንዳይሆኑ የባለሙያዎች ምክርና ድጋፍ እንዲሁም የጥንቃቄ ሥራ መጠናከር እንዳለበት፣ በሁለት ክልሎች መካከል ድንበር ተሸጋሪ የሆኑና የመጥፋት አደጋ ላይ ያሉ ብሔራዊ ፓርኮች ለማውጣት በፌዴራልም ሆነ በክልልም መሠራት የሚገባው ሥራ ያልተሠራ በመሆኑ ለሚመለከታቸው የብሔራዊ ክልላዊ መንግስታት ኃላፊዎች በጋራ ዕቅድ የመጨረሻ እልባት እንዲሰጥ፣ የኮሚዩኒኬሽን ስትራቴጂያችን አስተካክለን መስህቦቻችንን ለማስተዋወቅ ከምንጠቀምባቸው የማስተዋወቂያ ዘዴዎች ወጣ ብለን ቴክኖሎጂዎች ተጠቅመን በጥቂት ሰኮንዶች የሚተላለፉ የቪዲዮ መልዕክቶችን፣ ዜናዎችን በማህበራዊ ሚዲያዎች፣ ፌስቡክ፣ በዜና አውታሮች፣ በታብሌቶች፣ በሞባይሎች በመልቀቅ ህብረተሰቡም በቀላሉ እያየ የጉብኝት ባህሉን ማሳደግ የሚቻልበት ሁኔታ NEWSመመቻቸት እንደሚገባው፤ ከዚህ ቀደም በቱሪዝም ሀገራዊ ትራንስፎርሜሽን ለማምጣት ያስቀመጣናቸው ሶስቱ ፕላሮች  የማስፈጸም አቅማችንን ፈትሸን አሁንም ያልተሠሩ በርካታ ነገሮች በመኖራቸው ተሠርተው ለሚቀጥለው ጉባኤያችን እንዲቀርቡ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተሰጡት አቅጣጫዎች ዋና ዋናዎቹ  ናቸው፡፡

በመጨረሻም የኢትዮጵያ ቱሪዝም አባት በመሆን የሚታወቁት የ91 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ ለአቶ ኃብተሥላሴ ታፈሰ የሚኒስቴር መስሪ ቤቱ ያዘጋጀው የእውቅና ሰርተፊኬት፣ የክብር ሜዳሊያና የብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር) ሽልማት በኢፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከተበረከተላቸው በኋላ የጉባኤው ፍፃሜ ሆኗል፡፡


News and Updates News and Updates