News and Updates

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከቱሪዝም ዘርፍ የህዝብ ክንፍ ጋር ለመተዋወቅ እና በዘርፉ ያሉ ተግዳሮቶችን ለመለየትና አቅጣጫ ለማስቀመጥ ግንቦት 12 ቀን 2010ዓ.ም በጌትፋም ኢንተርናሽናል ሆቴል የምክክር መድረክ አካሄደ፡፡

የምክክር መድረኩን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ባህልና ቱሪዝም ሚንስትር ክብርት ወ/ሮ ፎዚያ አሚን በንግግር የከፈቱ ሲሆን በፌዴራል ደረጃ ተደራጅተው ከሚንቀሳቀሱ የህዝብ ክንፍ ጋር በጋራ ተሳስሮ የተሻለ ስራ ለማከናወን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር፣ የአሰራር እና የመመሪያ ክፍተቶች ላይ በመመካከር ችግሮችን የጋራ በማድረግና በመግባባት ለቀጣይ ስራ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ነው ብለዋል፡፡

የላልይበላን ጉብኝትና ውይይት በተመለከተ የተዘጋጀ ዜና ለአስተያየት የቀረበ

ክብርት ወ/ሮ ፎዚያ አሚን የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚንስትር የቅዱስ ላልይበላን ውቅር አብያተ ክርስትያናት ጠግኖ ከተጋረጠባቸው አደጋ ለመታደግ የተጀማመሩ ስራወችን ለመመልከትና ትኩረት ሰጥቶ ለመምራት የሚረዳ ጉብኝትና ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ውይይት አደረጉ።

ምርትና አገልግሎትን ስናስተዋውቅ ተጠቃሚዎቻችንን ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆን እንደሚኖርበት ተጠቆመ፤

ምርትና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የምንጠቀመውን ዘልማዳዊ የቋንቋ አጠቃቀምን ለመፈተሸ እና በቀጣይም ተገቢ የእርማት እርምጃ ለመውሰድ ያስችል ዘንድ ‘’የምርት እና አገልግሎት አቅርቦት ከህብረተሰቡ የቋንቋ አጠቃቀም አኳያ’’ በሚል ርዕስ ሰኔ 5/2010

በተደራጀ የወጣቶች ተሳትፎ ለባህል እና ቱሪዝም ልማት ወሳኝ ነው፤

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የሴቶችና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት “በተደራጀ የወጣቶች ተሳትፎ ለባህልና ቱሪዝም ልማት" በሚል መሪ ቃል ከደቡብ ብ/ብ/ሕ/ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመቀናጀት በባህልና ቱሪዝም ዘርፍ ለሚገኙ ከ9ኙ ብሔራዊ ክልሎች እና የሁለቱ የከተማ አስተ

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከወሎ ዩኒቨርስቲ ጋር በጋራ በመሆን በባህል ኢንዱስትሪ ምርቶች፤ አገልግሎቶች ገበያ ልማት እና ትስስር ስልቶች የጥናት ላይ የተዘጋጀ የጥናትና ምርምር መድረክ ከግንቦት 24-25/2010ዓ.ም በደሴ ከተማ ወሎ ዩኒቨርስቲ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡

በባህል ኢንዱስትሪ ምርቶች፤ አገልግሎቶች ገበያ ልማት እና ትስስር ስልቶች በጥናትና ምርምር መታገዝ አለበት፡፡ ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ (በወሎ ዩኒቨርስቲ የቢዝነስ ልማትና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ም/ል ፕሬዝዳንት) በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ በባህል ኢንዱስትሪ መስኮች እና አገልግሎቶች የገበያ ልማት ስልቶች በጥናትና ምርምር መታገዝ እዳለበት ገልጸዋል፡፡